የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር የፕሮጀክት ሽግግርና ማጠቃለያን በማስመልከት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የውይይት መድረክ አካሂዷል።በመድረኩ የስደት ተመላሾችን በሟቋቋም ሂደት የነበሩ መልካም ዕድሎችና ፈተናዎችን የዳሰሰ ጥናታዊ ሰነድ እና የሥራ ቡድኖች አደረጃጀት እና አሠራርን ለመወሰን የወጣ የማቋቋሚያ ደንብና አዋጅ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።በመድረኩ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከስደት ተመላሾችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር ያከናወናቸው ተግባራት በቢሮው የሥራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ሰብሀዲን ሱልጣን ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።ውይይቱን የመሩት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የቢሮው ሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው መላኩ ቢሮው ከስደት ተመላሾችን በዘላቂነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋልአቶ አስፋው አያይዘውም ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል የውጪና የአገር ውስጥ አሠሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን በቅርብ ሆኖ የመደገፍ፣ የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራ ትኩረት ተሠጥቶት ይሠራል ብለዋል።መጨረሻም በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎትና የስደተኞች ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ ምኞት ደራራ አማካይነት ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር የስደት ተመለሰች ፕሮፋይል ሰነድ ርክክብ ተከናውኗል።
.