ሚያዝያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
ብቁ፣ንቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡
በአዲስ እየተተገበረ የሚገኘው የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እና ስራ ፕሮጀክት አካል የሆነው ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት አተገባበር ማንዋል እና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የቴክኒክ ኮሚቴዎች እና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በሥራና ክህሎት ቢሮ የስራ ስምሪት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር #አቶ ሰባህዲን ሱልጣን ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ብቁ፣ንቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት ሂደት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ወጣቶች በስራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ በማድረግ በተለያዩ ድርጅቶች በቋሚነት እንዲቀጠሩ ያስችላል ሆኖም በልምምድ ወቅት የሚያጋጥመውን የማቋረጥ ምጣኔ ለመቀነስ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግም #አቶ ሰባህዲን ገልፀዋል።
ስልጠናው በፕሮጀክቱ አተገባበር ያለውን አፈፃፀም በመገምገም መሰረታዊ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደሚያግዝ እና በበጀት አመቱ ቀሪ ጊዜያት በሚከናወኑ ተግበራት ላይ እንደሚያተኩር ተጠቁሟል፡፡
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ አሁን ላይ 15 ሺ ወጣቶችን ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ49 ሺ የሚሆኑ የከተማችን ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በስልጠናው ተገልጿል፡፡
.