Home የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት አዲስ ያበለፀገውን ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት አዲስ ያበለፀገውን ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ።

08th July, 2024


ሰኔ 23/2016 ዓ ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያይዙ የሚስተዋሉ የአሠራር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ቴክኖሎጂ በማበልፀግ ተግባራዊ አድርጓል።
ቴክኖሎጂውን የፈጠረው የክ/ከተማው ባለሙያ ወጣት አባይ የመረጃ ድግግሞሽና ወቅታዊ አለመሆን፣ የውሸት ሪፖርት፣ ሪፖርት ለማዘጋጀት የሚፈጀው ጊዜ ረጅም መሆን እና መሰል ችግሮች ቴክኖሎጂውን ለማበልፀግ ምክንያት እንደሆነው አብራርቷል።
ቴክኖሎጂው ይፋ ሲደረግ የተገኙት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በእያንዳንዱ የመንግስት አገልግሎት ቴክኖሎጂን መጠቀም ሥራን ለማቅለል ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ሌሎች የክ/ከተማው ጽ/ቤቶች ከሥራና ክህሎት ልምድ በመውሰድ አሠራራቸውን ለማዘመን ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።
የክ/ከተማው ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም በክ/ከተማው የበለፀገው ቴክኖሎጂ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ከሚገኘው የLMIS ሥርዓት ጋር ተናቦ የሚሄድ እና በዚሁ ሥርዓት ያልተካተቱ አሠራሮችን አቅፎ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል።
የበለፀገው ቴክኖሎጂ ፀጋን ከመለየ ጀምሮ ያሉ የሥራ ሥምሪት ተግባራትን፣ የኢንተርፕራይዞች ድጋፍን፣ የክህሎት ስልጠና፣ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን እና ሌሎች መረጃዎችን በአንድነት አካቶ የያዘ እና ለአጠቃቀም ቀላል እና ግልፅ መሆኑ ከመድረኩ ተመላክቷል።
.

Copyright © All rights reserved.