Welcome to TVET
+25191 600 8638
|
arul@ree.org
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Home
News
Back
News
Event
Notice
College
More
Admission
CoC Result
Announcement
Resource
Legal
Education Statistics
Publication
Map
Support
Submit Ticket
My Tickets
Gallery
FAQ
About
Contact
College
College_mapping
Placements
Login
Home
ቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል የቴክኖሎጂና የፋሽን ውጤቶች አውድ ርዕይ ተከፈተ፡፡
ቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል የቴክኖሎጂና የፋሽን ውጤቶች አውድ ርዕይ ተከፈተ፡፡
08th July, 2024
ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ኮልፌ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ 14ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን በማስመልከት በኮሌጁ የተሰሩ የቴክኖሎጂና የፋሽን ስራዎች ለእይታ ክፍት አድርጓል፡፡
አውደ
ርዕዩን የከፈቱት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በሀገራችን በክህሎት እና በቴክኖሎጂ ብቁ የሆኑ ዜጎችን በማፍራት ምርታማነት እየጨመረ እንደሚገኝ ገልጸው በዘርፉ ክህሎት ያለው ለሀገር እድገት ወሳኝ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አቶ ንጋቱ ጨምረውም ኮሌጁ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚበረታቱና የክፍለ ከተማው አስተዳደርም በጋራ በሚሰሩ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡
የኮሌጁ የሰልጣኞች ልማት እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ወ/ሮ ትግስት አይናለም ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ኮሌጁ ከተቋቋመ ባለፉት 8 ዓመታት የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ቴክኖሎጂ ስራዎችን መስራቱን አስታውሰው አውድ ርዕዩ ኮሌጁ እየሰራ የሚገኘው ስራዎች ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ዓላማ አለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በአውደ ርዕዩ በኮሌጁ የተሰሩ የሻምፖ ማምረቻ፤የብረት መጠምዘዣ፤የሸክላ መፍጫ፤በቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ መጠቀም የሚያስችል የከሰል መስሪያ ቴክኖሎጂ ስራዎች፤የእንጨትና የፋሽን ውጤቶች ለእይታ ቀርቧል፡፡
በአውደርዕዩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፤ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም መሀመድ፤ የአካባቢው ባለድርሻ አካላት፤ አሰልጣኞችና ሰልጣኝ፤ የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል፡፡
አውድ ርዕዩም ለተከታታይ 3 ቀናት ይቆያል፡፡
ምንጭ:- ኮልፌ ኮሚኒኬሽን
.