Welcome to TVET
+25191 600 8638
|
arul@ree.org
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Home
News
Back
News
Event
Notice
College
More
Admission
CoC Result
Announcement
Resource
Legal
Education Statistics
Publication
Map
Support
Submit Ticket
My Tickets
Gallery
FAQ
About
Contact
College
College_mapping
Placements
Login
Home
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
08th July, 2024
ሰኔ 29/2016 ዓ.ም
በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በከተማ አቀፍ ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
በመዲናዋ “የምትተክል ሀገር- የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ከንቲዋን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተጀምሯል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተጀመረው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች ባደረጉት ንግግር፣ “ከተማችንን አረንጓዴ የምናደርጋት እኛው ነን፤ ይህንን የምናደርገው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው" ብለዋል።
የምንተክለው ችግኝ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ መተባበርን እና አብሮ መኖርን ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል።
አዲስ አበባ በየዓመቱ የምትተክላቸውን ችግኞች ቁጥር እያሳደገች መምጣቷን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ ባለፈው ዓመት 17.5 ሚሊዮን ተክለናል፤ ዘንድሮ 20 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እንሠራለን ብለዋል።
ዛሬ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩ ክረምቱን ሙሉ የሚዘልቅ መሆኑን ገልጸው፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ባለሃብቶች፣ ዲፕሎማቶች እና ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል።
"የምንተክለው የጥላ ዛፍ፣ ምግባችንን፣ የአየር ፀባይ ለውጥ መከላከልን፣ ጤናችንን ጭምር ነውና ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን የተከልነውን እንደ ልጆቻችን በመንከባከብ ውጤታማ ልናደርጋቸው ይገባል" ሲሉም አሳስበዋል።
ምንጭ:- አዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
.