Home በስራ እድል ፈጠራ ክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ።

በስራ እድል ፈጠራ ክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት እንደሚገባ ተገለፀ።

08th July, 2024


ሰኔ 23 ፤ ቀን 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ላለፉት 18 ቀናት ሲያካሂድ በቆየው እና 55 ወረዳዎችን በዳሰሰው የሥራ ዕድል ፈጠራ ክዋኔ ኦዲት ላይ ከክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና ስራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ፤ምክትል ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ከኦዲት ቡድን አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፤የጉለሌ ክፍለ ከተማ የተመረጡ ወረዳዎች እንዲሁም የ11 ወራት የሥራ ዕድል ፈጠራ ማጠቃለያ ክዋኔ ኦዲት የተገኙ ግኝቶች ቀርቧል።
በክዋኔ ኦዲት ስራው ለመዳሰስ ከታቀደው ወረዳ መያዝ ያለባቸው፤ መያዝ የሌለባቸው፣በመቀነስ እና በመጨመር የተመዘገቡ ቁጥራዊ መረጃዎች ተመላክተዋል።
በስራ እድል ፈጠራ ክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋት እንደሚገባ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የስራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ #አቶ አስፋው ለገሰ ገልጸዋል።
ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን ትርጉም ባለው መንገድ በተግባር ለማዋል ቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራ ስራውን ክዋኔ ኦዲት ማከናወኑ የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት የውይይቱ ተሳታፊዎች ቋሚ የስራ ዕድልን በመፍጠር ሂደት አቅጣጫ ያመላከተ መሆኑን ተናግረዋል።
.

Copyright © All rights reserved.