Home የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የካይዘን አሠራር

የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የካይዘን አሠራር

04th April, 2024

የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የካይዘን አሠራርን በተደራጀ እና ወጥ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተጠየቀ።
መጋቢት 20/2016 ዓ ም
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በስሩ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የካይዘን አፈፃፀማቸውን የተመለከተ የኦዲት ሪፖርት ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የኮሌጆች የካይዘን አፈፃፀም በፌደራል የካይዘን የልህቀት ማዕከል አማካይነት ኦዲት ሲደረግ ቆይቶ የኮሌጅ ዲኖች፣ የቢሮው ባለሙያዎች፣ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኦዲት ግኝት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
ውይይቱን የመሩት በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የቢሮው አማካሪ አቶ ቸርነት በላቸው ኮሌጆች በኦዲት የተለዩ ክፍተቶችን በዕቅድ አካተው ሊያርሙ እንደሚገባ ገልፀው ሁሉም ኮሌጆች የካይዘን አሠራርን በተደራጀ እና ወጥነት ባለው መልኩ ሊተገብሩ ይገባል ብለዋል።
በቢሮው የተቋማት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምባቸው ግርማይ የውይይቱ ዋና አላማ ኮሌጆች እርስበእርስ እንዲማማሩ በማድረግ ቀጣይነት ያለው የካይዘን አፈፃፀም ሥርአት እንዲኖራቸው ማስቻል ነው ብለዋል።
.

Copyright © All rights reserved.