Home የሥራ ዕድል ፈጠራ

የሥራ ዕድል ፈጠራ

04th April, 2024

"በየደረጃው የሚገኘውን ፈፃሚ በአመለካከት መቀየር፣ በስልጠና ማብቃት እና ስምሪት ሰጥቶ መከታተል ወሳኝ ነው"። ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሦስት ወር የንቅናቄ ዕቅድ የ54 ቀናት አፈፃፀምን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ከቢሮው የማነጅሜንት አባላት፣ ከክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና ከሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊዎች ጋር የዘጠና ቀናትን የንቅናቄ ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግመዋል።
አቶ ጥራቱ በየነ በግምገማው ማጠቃለያ በሰጡት ሀሰብ አመራሩ በየደረጃው የሚገኙ ፈፃሚዎችን በአመለካከት መቀየር፣ በስልጠና በማብቃት እና ስምሪት ሰጥቶ በመከታተል ቀሪ የንቅናቄ ስራዎችን ለማሳካት በትኩረት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።
አቶ ጥራቱ አያይዘውም የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ለማሳካት ለአመራር ስምሪት በቂ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ ይገባል በማለት አቅጣጫ ሰጥተዋል።




.

Copyright © All rights reserved.